የፍኖተ ዴሞክራሲ የኢትዮጵያ አንድነት ድምጽ (ጥቅምት 8 ቀን 2008 ዓ.ም የተላለፈ): ከግማሽ ምዕተ- ዓመት ያላነሰ ትግል ሲያካሂድ የቆየው ትውልድ፤ በተፈጥሮ ህግ ምክንያት፤ ቀስ በቀስ ሳያውቀው በሞት እየተለየ በመሄድ ላይ ይገኛል። ተኪውን ሳያዘጋጀ ቢያልፍ አገሪቱ ከባድ አደጋ ውስጥ ትወድቃለች። ይህ ትውልድ ሳይተካ ከሄደ፤ ሀገሪቱ መፃዒ እድሏን ሊረከብ የሚችል ትውልድ እያጣች ትሄዳለች ማለት ነው። ስለሆነም በዚህ በኩል መፍትሔ መፈለግ ይኖርበታል። ለዚህ መፍትሄ ካልተገኘ ደግሞ፤ ሀገርን ማዳን ቀርቶ ራስንም እንኳን ቢሆን ከአደጋ መከላከል የሚቻል አይሆንም። የታጋዮች መዳከም ወያኔ፤ ጠላቶቹን፤ ለየብቻ እየነጣጠለ ለመምታት ምቹ ሁኔታ የፈጠረለት ሲሆን የወጣቱን ትውልድ አዕምሮ ለመስረቅ ዕድል ገጥሞታል። የተተኪውን ትውልድ አዕምሮ ከመስረቅ የበለጠ፤ ሀገር የማጥፋት ወንጀል ደግሞ ሊኖር አይችልም። ሙሉውን ያንብቡ