በስደት የኢትዮጵያ መምህራን ማኅበር አባላት አስተባባሪ ኮሚቴ: ከመምህራን ጋር ፡-በአንዳንድ አካባቢዎች በህዳር ወር 2007ዓ.ም መጀመሪያ ሳምንት በተደረገ የመምህራን ስብሰባ ከ2006ዓ.ም በፊት በነበሩት አመታት ትምህርታቸውን ያቋረጡ ተማሪዎች እስከ ህዳር ወር መጨረሻ 2007ዓ.ም ድረስ ትምህርት ቤት እንዲገቡ የሚል ሐሳብ በወያኔ ካድሬዎች ይቀርባል።ለዚህ የተሰጠው ምክንያት የምዕተ ዓመቱ ( የሚሊኒየሙ) የልማት ግብ በዚህ በያዝነው አመት ስለሚጠናቀቅ አሁን በመማር ላይ ያሉት መማር ከሚገባቸው ተማሪዎች ቁጥር ያነሰ በመሀኑ ያቋረጡትን “በቅስቀሳ “ በማምጣት ከመስከረም 2007ዓ.ም ጀምሮ እየተማሩ ካሉት ጋር እኩል ማድረስና የምዕተ ዓመቱን “ ትምህርት ለሁሉም” የሚለውን ግብ ማሳካት በሚል የቀረበ አጀንዳ ነበር። ሙሉውን ያንብቡ