ዴሞ፣ ቅጽ 42፣ ቁ. 5 (መጋቢት/ሚያዚያ 2009 ዓ.ም.) – በዛሬዋ ኢትዮጵያ ከሚታየው ጠቅላላ ገፅታ አንፃር፤ የጠላቶቿ ሴራ ተሳክቶላቸዋል ከማለት አንቆጠብም። ይህን ስንል፣የነርሱ ብርታትና ብልሃት ሳይሆን፤ የራሳችን ድክመትና እንዝህላልነት ያስከተለብን ጣጣ ነው። እንዲያውም የሀገራችን ጠላቶች ብዙ ሳይደክሙ፤ የፈለጉት ተሟልቶላቸዋል፡፡ ይህን ዕውነታ፤ እንደ እንቆቆ እያንገሸገሸን ነው የምንናገረው። ዘጠና ስድስት ሚሊዮን ሕዝብ፤ የአንድ ሰፈር ልጆች መጫወቻ ሲሆን ማየት፤ እጅግ ሲበዛ ያንገፈግፋል። የስድሳ ስድስቱ አብዮት ዓላማና ግቡን ሳይመታ ትግላችንን አናቆምም ስንል፤ ከዚህ የማይፋቅ ዕውነትና ዕምነት በመነሳት ነው። የዕምነት ግማሽ የታሪክ ቅናሽ የለንም። ወያኔ በውጭ ኃይሎች የእዝ ጠገግ ሥር መሆኑ ብቻ ሳይሆን፤ የዛፍ ላይ ዕንቅልፍ የሚያንጎላች ቡድን በመሆኑ፤ ቅዠት እንጅ ህልም እንደሌለው እናውቃለን። በቅዥት የሚኖር ስብስብ በመሆኑም ሌላውን ቀርቶ፤ የራሱን ጥላ እንዃ የሚፈራ ቡድን ነው። ማንንም ሊያምን አይችልም። እውነት መልኳን ብትለውጥ እንጅ፤ ጠባይዋን ስለማትስት ከኢትዮጵያ ሕዝብ ትግል ጎን ቆማ፤ ሀቁን እየተናገረች ሀገራዊ ድሉን ታበስራልች! ያ ድል እስከሚመጣ ድረስ ትግላችንን እንቀጥላለን! ሙሉውን እትም ያንብቡ…