ፍጹም መንገሻ (ኖርዌይ): በሃገራችን እንደ አለመታደል ሆኖ ህዝብን የሚወክል በህዝብ የተመረጠ መንግስት ሳይኖረን ይህንን እድል ለመፍጠር እድሉ የነበራቸውም ቡድኖችም ሆኑ ግለሰቦች ከህዝብ ፍላጎት እና ከሃገር ጥቅም ይልቅ የግል ጥቅማቸውን እና የባእዳኖችን ፍላጎት በማስቀደም ያገኙትን የተለያዩ አጋጣሚዎችን በመጠቀም የህዝብን ስልጣን እየነጠቁ ለህዝብ እና ለሃገር የቆሙትን እየገፉ እና እየገደሉ በጉልበት መንግስት ነን እያሉ ህዝብን በማገልገል ስራ ሳይሆን የየራሳቸውን ጥቅም በማስጠበቅ እና በስልጣን ለመቆየት እንደተጠመዱ የህዝብን ሃብት ለግል ጥቅማቸው እያዋሉ ህዝብን እንዳሻቸው እየጨቆኑ እያንገላቱ ቆመንለታል የሚሉትን ህዝብ እየጨፈጨፉ ሃገርን እየጎዱ ለትውልድ የሚተርፍ ታሪክ የማይረሳው የጥፋት አሻራ ጥለው ያለፉ እና እያለፉ ያሉ የተለያዩ ስርዓቶችን እያስተናገደች አለች።ከነዚህም ውስጥ አንዱ ከፋሺስት ደርግ ስልጣኑን የተረከበው አሁን በስልጣን ያለው ዘረኛው የወያኔ ስርአት ነው። የፋሺስት ደርግ ስርዓት ለሃገር እና ለህዝብ የቆሙትን በመጨፍጨፍ እንደሚታወቀው ሁሉ አሁን በአገዛዝ ያለው ስርዓትም የራሱ የሆነ ጸረ ህዝብ እና ጸረ ሃገር የሆኑ መለያዎች አሉት። ሙሉውን ያንብቡ