ግንቦት 14 ቀን 2007 ዓ.ም.: በአገር ቤትና በጎረቤት አገሮች በሳተላይት የሚሰራጨው የፍኖተ ዴሞክራሲ የኢትዮጵያ አንድነት ድምጽ ራዲዮ ዝግጅት ትናንት ሐሙስ ግንቦት 13 ቀን 2007 ዓ.ም. መቋረጡን ተረድተናል። ፕሮግራሙ የተቋረጠው ሳተላይቱና የሚያሰራጨው ኩባንያ (Nilesat) የተመዘገበበት አገር (ግብጽ) መንግስት በኩባንያው ላይ ባደረገው ተጽእኖ መሆኑን መረጃ የደረሰን ሲሆን ተጽእኖ በምን ምክንያት ሊደረግ እንደቻለና ስርጭታችን ወደ ፊት በምን መልክ ሊቀጥል እንደሚችል የሚያብራራ ተጨማሪ መረጃ እንደደረሰን ለአድማጮቻችን እንገልጻለን። የበለጠ ያንብቡ