ከነፃነት በቀለ፡ በየዕስር ቤቶቹ በሺዎች ታጉረው እያሉ “ እኔ እንዳርጋቸርው ነኝ”፣ “አንዳርጋችው ይፈታ” ለማለት እዚህም እዚያም ሰልፍ ይወጣል፡፡ ባንዳንድ አካባቢ ደግሞ አዳማጭም ተመልካችም በሌለበት ይወጣል፡፡ መሰረታዊ አላማው ፍጹም አልተስተካከለም፡፡ መፈክሩ መሆን ያለበት “ያለአግባብ የታሰሩ በሙሉ ይፈቱ” ነው፡፡ የሚናከስ ስራ ከሰራን ሺዎቹ ይፈታሉ፡፡ አንዳርጋቸው ከሺዎቹ ውስጥ ይሆናል፡፡ አንዳርጋቸውን ማስፈታት በሺህ የሚቆጠሩትን አያስፈታም፡፡ የሺዎቹ መፈታት በአንድ አንዳርጋቸው መፈታት ይተረጎማል ካልተባለ በስተቀር፡፡ ያም ይሁን ይህ ዛሬ በኢትዮጵያችን የታገቱት ከ40,000 በላይ እንደሆኑ ይነገራል፡፡ አንዳርጋቸው ቢፈታ 39,999 ምስኪን እስረኞች እዚያው በሰው በላው ወያኔ እየተሰቃዩ የእስር ቤት ህይወታቸውን ይቀጥላሉ፡፡ የሚከብድ ስሌት አይመስለኝም፡፡ ሙሉውን ጽሑፍ ያንብቡ …