የፍኖተ ዴሞክራሲ የኢትዮጵያ አንድነት ድምጽ ሀተታ (ነሐሴ 12 ቀን 2007 ዓ.ም. የተላለፈ): አዳዲስ ኃሳብ ማመንጨት የተሳነው ኅብረተስብ፤ ሁል ጊዜ በቆየውና ባሮጌው ጉዳይ ላይ ሲያመነዥግ ጊዜውን ያሳልፋል። ያንኑ በመደጋግም ፤ እያዘዋወረ፤ እያፍተለተለና እያውጠነጠነ ከመኖር የተሻለ አዲስ ኃሳብ ለማምጣት አልታደለም። አሮጌውን በመቀባበል ብቻ የሚረካ ኅብረተሰብ፤ “እልፍ ሲሉ ዕልፍ እንደሚገኝ” እንኳን አይገነዘብም። በልተውና ጠጥተው ከተገለገሉበት በኋላ እንደገና ለመገልገል የሚፈልጉትን የወረቀት ሳህንና ዋንጫ (Recicle/ ሪሳይክል ) እያዟዟሩ መኖር፤ የፈጠራ ክኅሎትን አያበረታታም።
አባቶችና እናቶች ባስመዘገቡት ታሪክ ብቻ እየተኮራሩ መኖር ፤ የትም እንዳላደረሰን፤ አሁን የወደቅንበት ሁኔታ በቂ ማስረጃ ሆኖብናል። ይህ ትውልድ፤ የራሱን ችግር አስወግዶ፤ መፃዒ ዕድሉን የሚያመቻች ተግባር መፈፀም ካልቻለ፤ የአምባገነኖች ሰለባ መሆን ብቻ ሳይሆን፤ በድኅነት አረንቋ ውስጥ ተዘፍቆም ይኖራል። የዓለም ኅብረተስብ መሳቂያ መሳለቂያ ከመሆንም አይድንም። የሀገራችንም ዕድል፤ ተስፋው ብርሃን አይገኝም። ዝም አይነቅስም በመሆኑ፤ ሁሉን በዝምታ ማሳለፍ ተመርጧል። ሙሉውን ያንብቡ