የፍኖተ ዴሞክራሲ የኢትዮጵያ አንድነት ድምጽ ሀተታ (ግንቦት 23 ቀን 2007 የተላለፈ): ለረዥም ጊዜ፤ ወያኔ፤ የቀልድ ምርጫ ለማድረግ የሚያስችለውን መስናዶ ካደረገ በኋላ፤ ብቻውን ሮጦ ራሱን በመቅደም አቸንፌአልሁ ብሎ በዚህ ሳምንት አውጇል። ይህንን እንደሚያድርግ ደግሞ ያልተጠበቀ አልነበረም። ደጋፊዎቹና አሽቃባጮቹም አጨብጭበውለታል። የበላይ ጠባቂዎቹና ዐለቆቹም “አባጀህ ልጃችን!” ብለውታል። የአገልጋይነት ዘመኑን እንዲራዘምላቸው ማረጋገጫ ስላገኙም፤ በደስታ ፈንድቀዋል። ኢትዮጵያና ዜጎቿ፤ ወደ ሌላ የመከራ አጋዛዝ መሸጋገራቸውን ግን አልተረዱትም። ሊረዱትም አይችሉም። ቀድሞውንም ቢሆን፤ ጉዳያቸው አልነበረምና! ሙሉውን ያንብቡ