የፍኖተ ዴሞክራሲ የኢትዮጵያ አንድነት ድምጽ ሀተታ (ሚያዚያ 29 ቀን 2007 ዓ.ም. የተላለፈ): በዚህ ባሳለፍነው ሣምንት፤ የኢትዮጵያ ሕዝብ ፤ ከዳር አስከ ዳር በአንድ ላይ በመውጣት፤ እንደ በግ የታረዱበትን ልጆቹን አሰቃቂ ሞት መሪር ሀዘኑን ተወጥቷል። በዓለም ዙሪያ የተሰደደው ዜጋ ሁሉ ምሬቱን፤ ሀዘኑን ሲገልጽ ቆይቷል። በበርካታ ኪሎ ግራም የሚመዘን የመታሰቢያ ሻማ በርቷል። ተቃጥሏል። ለቁጥር የሚታክቱ የተቃውሞ ሰልፎች በዓለም ዙሪያ ባሉ ከተሞች ተካሄደዋል። ሙሾዎች ተደርደረዋል። አንጀት የሚበሉ የሀዘን ግጥሞች ተጽፈዋል። ኤሎሄ ኤሎሄ! እየተባሉ ተነብበዋል። በመላው ዓለም የሚገኙ የሀይማኖት ተቋማት የሀዘን ጸሎት አድርሰዋል። የሰብዓዊ መብት ተከራካሪዎች የውግዘት መግለጫ አትመዋል። ሀገር- ወዳድ ኢትዮጵያውያን ምሁራንም፤ ቀስቃሽ- አነሳሽ ጽሁፍ ለታረዱት ወገኖቻችን መታሰቢያ አበርክተዋል።
በሀዘን ልቧ የተሰበረው፤ አንዲት- እስላም ኢትዮጵያዊት ወጣት ሴት፤ በዕንባ የታጠበውን ፊቷን እያበሰች፤ ወንጀለኞቹ ን በሚገባቸው፤ በዐረብኛ ቋንቋ፤ ቅዱስ ቁርዓንን እየጠቀሰች አውግዛቸዋለች። ስሟ ኢክራም ትባላለች። የሀገሯ ኢትዮጵያንና የሕዝቧን ፍቅር ለመግለጽ ተንሰቅስቃ አልቅሳለች። የተመልካቿንም ልብ በልታለች።
” እናንተ አረማውያን፤ የገደላችኋቸው፤ ሠላሣ ወገኖቻችንን ብቻ አይደለም። መላውን የኢትዮጵያን ሕዝብ ጭምር እንጅ ” ብላቸዋለች። እናንት ነጃሳዎች፤ ጀሃነም {ገሃነም} ትገባለችሁ ” ብላ ረግማቸዋለች ። ቅዱስ ቁርዓንንና ኤል ሃዲስ መፃሃፍን እየጠቀሰች፤ ” ሀበሻን አትንኳት የተዳፈነች እሳት ነችና ታቅጥላችኋለች ” ( ከሊሃ ኤል ሀበሽ ወ ህያ ኤል መካን ሚን ወለኣ ) ብላ በድፍረት ተገፍጣቸዋለች። ስሟንም ደፍራ ተነግራ ፤የሚከተልባትን አደጋ ሳትፈራ፤ ቆራጥ ኢትዮጵያዊት መሆኗን አረጋግጣ ነግራቸዋለች። መላው የኢትዮጵያ ሕዝብም አመስግኗታል፡፡ ኮርቶባታል። ሙሉውን ያንብቡ