ሊያነቡት የሚገባ ወቅታዊ ሐተታ፡ … ያለመታከት ደጋግመን እንደምናሳስበው፤ ሀገራችን እንደ ሀገር፤ ዜጎቿም እንደ አንድ ሕዝብ እንዳይኖሩ የመጨረሻው በር ከተዘጋ በኋላ፤ የኢትዮጵያን ተስካር ለማውጣት ተሰብስበን እንላቀስላት ማለቱ አይጥቅምም። ይህ እንዳይሆን አስቀድመን ብልሃት ይፈልግ ብለው የተናገሩትም ቢሆን ከተጠያቂነት ነፃ ይሆናሉ ማለት አይደለም። ይህንን ማስፈሩ፤ ለታሪክ ማጠያቂያነትና ማመሳከሪያነት ምናልባት ይረዳ ይሆናል ከሚል ቀቢፀ ተስፋ ሳይሆን፤ ዕውነቱ መነገር አለበት ከሚል የማረጋገጫ ግንዛቤ ነው። ያም ሆኖ፤ እየተጠራሞተች ያለችው ሀገራችን በምንም መንገድ ቢሆን የማደጎ ልጅ /ጉድፈቻ አትሆንም። የመጨርሻው ኢትዮጵያዊ ዐርበኛ ክንዱን እስከሚንተራስ ድረስ ሀገራችንን የመታደጉ ትግል መቀጠሉ አይቀርም! ልብ ያለው ልብ ይበል። ልብ ካለው ወገኑ ጋርም ልብ ለልብ ይግባባ! ልብ ለልብ ከተግባቡ የልባሞች ብልሃት ጠፍቶ አይጠፋምና! ሙሉውን ፅሑፍ ያንብቡ …