ከኢያሱ ዓለማየሁ: አንዳንዶች የአሜሪካ ሰርጎች ገቦች እጅ አለበት ብለው በሚጠረጥሩት የኢሕአፓ ሰራዊት ብተና ሂደት ሳቢያ የተበተኑት ተመልሰው በድርጅቱ እንዳይሰባሰቡ ማራቅ የሚል ዕቅድ ተጠንስሶና ለሱዳንም ቀርቦ ብዙዎቹን ወዲያውኑ ወደ አሜሪካ ማጓጓዝ–ማስፈር መካሄዱን እናውቃለን። ኢሕአፓም ብተናው ያደረሰበትን ችግርና ቀውስ ተቆጣጥሮ እንደገና ትግሉን ሲቀጥልም በጭልጋ ቋራ ጥቃት ሊያደርስበት በቀጥታ በሲአይ ኤ፤ ሻዕቢያና የሱዳን የሚሊቴሪ የስለላ ተቋም የተደራጀ ና አዳዲስ የቻይና መሳሪያ የታጠቀ ሀይል ኢሕአሠን ሊያጠቃ ሞክሮ ድባቅ ተመቶ ሴራው ከሽፏል። ግቡ የነበረው ኢሕአፓ/ሠ ን አጥፍቶ የነደረጀ ዴሬሳ ኢሕዴአ/ኢፒዲኤ ለመትከልና ሻዕቢያ በሚሰጣቸው የጦር አስረኞች ለማጠናከርና የኢፒዲኤንም ሱዳን የተተከለ ራዲዮ ወደ ሀገር ለማስገባት ነበር። ሻዕቢያና ሲአይ ኤ የደርግን ጦር ለነሻዕቢያ በሚያመች ደረጃ ለመከፋፈል ሳይጀመር ያለቀለት መፈንቅለ መንግስት አስሞክረው እንደነበር ሲታወቅ ለዚህም ተባባሪ የሆናቸው አረመኔው ኮለኔል አንጋፋ የጦር ጄኔራሎችን ገድሎ ያደረሰው ጉዳት ታሪክ ገና ዝርዝሩ የተነገረ አይደለም። በመፈንቅሉ ተሳትፈው ወደ አሜሪካ የሮጡ ጄኔራሎችም ዝርዝር መረጃና ዘገባ ለአሜሪካ እንጂ ለሚመለክተው ለኢትዮጵያ ሕዝብ አልሰጡም። ይህ ሁሉ ታሪክ አስተማሪና አልፎም አስጠንቃቂ ሆኖ እያለ ዛሬም አሜሪካን እንደ ወዳጅ መማጸን፤ አሜሪካ ቅጥረኛ ያደረገቻቸውን ታጋይ ብሎ በትከሻ መጫንና ሀገር ጎጂ መጃጃልን ማቀፍ ሰፍኖ ይታያል። ሙሉውን ያንብቡ