ከቦታቸው መፈናቀልን የተቃወሙ ኢትዮጵያዊያን እስራትና ግድያ እናወግዛለን!

 

ኢሕአፓ ወክንድ፡ ሰሞኑን ከአዲስ አበባ አቅራቢያ ያሉ ብዙ ከተሞችን በዋና ከተማው ስር ለመጠቅለል የወያኔ አጋዛዝ “ የተቀናጀ የልማት ማስተር ፕላን” በሚል ያወጣውን አቅድ፣ የማፈናቀል እርምጃ ነው ብለው በሰላማዊ መንገድ ተቃውሟቸውን ለማሰማት ሰልፍ የወጡ ዜጎችን በጅምላ ገድሏል፣ ብዙዎችን አቁስሏል፣ በገፍ አስሯል። በአምቦ ከተማ ብቻ አስካሁን በተገኙት መረጃዎች በትንሹ 47 የሚሆኑ የተገደሉና ብዙ የቆሰሉ ሲገኙበት፣ በጅማ ካምፓሶች፣ ወለጋ፣ መቱ፣ ቦሉ ሆራ፣ አዳማ ሃረሚያና በሌሎች አካባቢዎች ተመሳሳይ የጭካኔ አርምጃ ወስዷል። ኢሕአፓ-ወክንድ ይህን የወያኔ ኢሰብአዊ ድረጊት አጅግ በመረረ ቃል ያወግዛል።  ሙሉውን መግለጫ ያንብቡ …