ምንጮቻችን እንደገለጹልን ወያኔ በመላው ኢትዮጵያ የሚገኙ ብዙዎቹን የትግራይ ተወላጆችን 1 ለ 5 በሚል አደራጅቷል:: ይህም በአሻንጉሊቶቹ የተከበበት ኢህአዲግ ካለው መሰል አደረጃጀት ጎን ለጎን ነው:: እነኝሁ 1 ለ 5 የተደራጁት የወያኔ አባላትም ወደዱም ጠሉም ቢያንስ በሳምንት አንድ ጊዜ ለሚመደብላቸው ሰው ስለሚኖሩበት፣ ስለሚሰሩበት በአጠቃላይ ስላዩት፣ ስለሰሙት፣ ስለሰለሉት ዘገባ (ሪፖርት) ያደርጋሉ::
ባለፈው እሁድ ከተካሄደውና ወያኔ እራሱ ተወዳዳሪ፣ እራሱ ዳኛ ሆኖ ካሸነፈበት የቀልድ ምርጫ ጋር በተያያዘም 20 ሺህ የሚጠጉ የትግራይ ተወላጆች የሆኑ ሲቪሎች መሳሪያ ታጥቀዋል አዲስ አበባ ውስጥ:: እነኝሁ አባላትም የሚያወቋቸውን ሰዎች ሁሉ “ካርድ ወስደሃል? መርጠሃል ወይ?” ወዘተ የሚሉትን ጥያቄዎች በመጠየቅና በወግ መልክ በመሰለልና በመከታተል፣ ለተመደበላቸው የወያኔ አገናኛቸውም ዘገባ በማቅረብ ተጠምደው ሰንብተዋል:: ሙሉውን ያንብቡ