በስደት የኢትዮጵያ መምህራን ማኅበር አባላት አስተባባሪ ኮሚቴ: ብዙውን ጊዜ በዓለማችን በተፈጥሮ አደጋና በተላላፊ በሽታ ከሚያልቀው ሕዝብ ይልቅ በጥቅም ተናንቆ የሚያልቀው ቁጥር ሚዛኑ ይደፋል። ያለፉት ሁለቱ የዓለም ጦርነቶች ያሳዩት ይኽኑ ዕውነታ ነው። አንዱ ጥጋበኛና አምባገነን መንግሥት (አገር) ሌላኛውን አገር በጦርነት ወሮ የተጠቂውን አገር የተፈጥሮ ሐብት መዝረፍ፣የሕዝቡን ነፃነት መግፈፍና ለባርነት መዳረግ ያለንበት ዘመን ተጨባጭ ሁኔታ ባይፈቅድም ስልቱና መልኩ ተቀይሮ አሁንም ስቃይ መከራ እንዲቀበሉ የተፈረደባቸው ሕዝቦች አሉ። አገራችን ኢትዮጵያም የዚህ ግፍና በደል ሰለባ ሆናለች። ሙሉውን መግለጫ ያንብቡ