ዜና ፍኖተ

የካቲት 28 ቀን 2008 ዓ/ም:  በአዲስ አበባ የተጀመረውን በሌሎች የኢትዮጵያ ከተሞች የተካሄደው የታክሲዎች የሥራ ማቆም አድማ በዛሬው የካቲት 28 2008 ዕለት በጎንደር ውስጥ በጋይንት ተደረገ –  የአዲስ አበባው ሲኖዶስ ያደረገውን ድንገተኛ አስቸኳይ የቋሚ ሲኖዶስ ጉባዔ በዛሬው ዕለት አጠናቅቆ መግለጫ ያወጣል ተብሎ ይጠበቃል። በቋሚ ሲኖዶስ እና በፓትሪያርኩ መካከል ከፍተኛ የሆነ የአሰራርና የሃሳብ ልዩነት ያለ ሲሆን ቋሚ ሲኖዶሱ አቡነ ማትያስ በማኅበር ቅዱሳን ላይ ያስተላለፏቸው መመርያዎችና የጠሯቸው ስብስባዎች ሁሉ ህገ ወጥ ናቸው በማለት የተቻቸው ሲሆን ከእንግዲህ ወዲህ የቤተ ክርስቲያኒቱን መዋቅር ጠብቀው እንዲሰሩና ኃላፊነታቸው እንዲወጡ አስጠንቅቋቸዋል –  በኢትዮጵያ በተለያዩ ከተሞች ሲካሄዱ የነበሩ ሕዝባዊ ተቃውሞችን ለመግታት ተገቢ ርምጃ አልወሰዳችሁም የተባሉ ሁለት የኦህዴድ የማዕከላዊ ኮሚቴ አባላት ከኃላፊነት መነሳታቸው የሚታወስ ሲሆን በወያኔ አስገዳጅነት በሚካሄደው የወያኔ ኦህዴድ ማዕከላዊ ኮሚቴ ስብስባ ሌሎች ተጨማሪ የማዕከላዊ ኮሚቴ አባላት ሊባረሩ ወይም ሊታሰሩ ይችላሉ የሚል ግምት እየተሰጠ ነው – በተመሳሳይ ዜናም የወያኔው ብአዴን ማዕከላዊ ኮሚቴ አባላት በስብሰባና በግምገማ የተወጠሩ ሲሆን ከፍተኛ የብአዴን ካድሬዎች ከሥራና ከኃላፊነት ሊባረሩ ይችላሉ ተብሏል። የወያኔ መሪዎች የብአዴን መሪዎች ወያኔ ራሱ ያቀጣጠለው የቅማንት ማንነት ችግርን የብአዴን መሪዎች በአግባብ አልያዙም በሚል እየወቀሰ ሲሆን የወልቃይት እና የጠገዴ ወረዳዎችን ወደ ጎንደር እንዲቀላቀሉ ብአዴኖች ውስጣዊ ድጋፍ ሰጥተዋል ተብለው እየተወቀሱ ናቸው  – በኢትዮጵያ የተባበሩት መንግስታት የምግብ እና የእርሻ ድርጅት ተወካይ የሆኑት ሚስተር አህማዱ ለሚቀጥለው የመኸር ወቅት መዘጋጃ በርካታ አካባቢዎች ድጋፍ የሚያስፈልጋቸው መሆኑን ገልጹ – የቱኒዚያ የጸጥታ ኃይሎች ከሊቢያ በኩል ወሰን ጥሰው መጥተው ጥቃት ፈጽመዋል የተባሉ 21 የአይሲስ ታጣቂዎች መግደላቸውን አስታውቀዋል –  የሞሮኮ የአገር ግዛት ሚኒስትር ቃል አቀባይ ሰኞ የካቲት 28 ቀን 2008 ዓም በሰጠው መግለጫ ህዝብ የሽብር ተግባር ለማካሄድ ሲያቅዱ ነበር ያላቸውን አምስት የአይሲስ አባላት በቁጥጥር ስር ያደረገ መሆኑን ገልጿል። አሸባሪዎቹ ፕሬሸር ኩከር በመጠቀም በገበያ ቦታዎች ፈንጅዎችን ለማፈንዳት ሲዘጋጁ ተይዘዋል ያለው መግለጫ በሊቢያ በአይሲስ አማካይነት ተጨማሪ ወታደራዊ ስልጠና ለመቀበል እቅድ የነበራቸው መሆኑም ተገልጿል –  በሱማሊያ በላፕ ቶፕ ኮምፒውተር ላይ የተጠመደ ፈንጅ በአውሮፕላን ማረፊያ ፍተሻ ላይ እንዳለ በመፈንዳቱ ስድስት ሰዎች የቆሰሉ መሆናችው ተነገረ –  አሌክ ባዴ የሚባሉት የናይጄሪያ የቀድሞ የመከላከያ ሚኒስትር ሰኞ የካቲት 28 ቀን አስር በሚሆኑ የሙስና ክሶች ተከሰው በናይጀሪያ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የቀረቡ መሆናቸው ተገልጿል። ባዲህ 19.7 ሚሊዮን ዶላር የሆነ ገንዝብ በማጉደል የተከሰሱ ሲሆን ከክሶች ውስጥ አንደኛው በ2005 ዓም ለአየር ኃይል ከተመደበው በጀት ውስጥ 6.9 ሚሊዮን ዶላር ስርቀው በአቡጃ ውስጥ ከፍተኛ የሆነ የመኖሪያ ህንጻ አስርተውበታል የሚል ነው።

ዝርዝር ዜና:

ለማንበብ

ክፍል አንድን ለማዳመጥ

ክፍል ሁለትን ለማዳመጥ