ሊቁ እጅጉ እና አዳነ አጣናው: ዛሬ ኢትዮጵያን የሚመራው ሕዝባዊ ወያኔ ሐርነት ትግራይ(ወያኔ) ለይስሙላ እንደሚያናፍሰው ሳይሆን ከመጀመሪያ ሲመሠረት ታላቁን የትግራይ ሕዝብ ከወገኑና ከሀገሩ ኢትዮጵያ ገንጥሎ በአልባንያ ቅርፅ የተዋቀረች Socialist Democratic Republic of Tigray ለመመሥረት ነበር። ይህን ጠባብ አላማ የታቀወሙትን የትግራይ ሰዎች በግፍ አርዷል፣ ብዙዎች ለትምህርት ሄደዋል እየተባለ ቤተሰብ እንኳ በወጉ ሳይቀብራቸው በሺዎች የሚቆጠሩ በየጣሻው ወድቀው ቀርተዋል። ለዚህ እኩይ ዓላማ ከሀገሪቱ መደበኛ ጠላቶች ጋር አጥፊ ሴራዎችን በመጎንጎን በትግራይ ሕዝብና የሃይማኖት ተቋማት ላይ እጅግ የረቀቀና ጭካኔ የተሞላበት ግፍና በደል አድርሷል፣ ኢትዮጵያንና ታሪኳን እናስቀጥላለን በሚሉ የትግራይ ወገኖችና የሃይማኖት መሪዎች ላይ አረመናዊ ጭካኔ ፈጽሟል። ሙሉውን ያንብቡ