ከኢሕአፓ ወክንድ የተሰጠ መግለጫ: ደቡብ አፍሪካ ነፃነቷን ከተቀዳጀች በኋላ በተለያዩ ጊዜያት ሀገር ውስጥ በገቡ ዕና በላባቸው ጥረው ግረው በሚኖሩ ሰላማዊ አፍሪካውያን ስደተኞች ላይ የተለያዩ ዘረፋዎችና ነብስ ግድያዎች ሲካሄዱ ቆይተዋል፡፡ አሁን ደግሞ ይባስ ብሎ የሰውን ልጅ ከነ ህይወቱ በእሳት ሲቃጠል መንግስትና ህግ ያለበት ሀገር እሰከማይመስልም ድረስ በገጀራ ተጨፍጭፎ ሲገደል ማየት ለህሊና የሚዘገንን አረመኔ ተግባር ነው፡፡ እጅግ የሚያሳዝነው ደግሞ ይህንን ኢ-ሰብዓዊ ተግባር እየፈፅሙ ያሉ የሀገሪቱ ዜጎች ትናንት በፀረ-አፓርታይዱ ትግል ከጎናቸው በመቆም ከኔልሰን ማንዴላ ጀምሮ እስከ የአፍሪካ ብሄራዊ ኮንግረስን ተዋጊ ክንፍ በማሰልጠን፣ እንዲሁም በዲፕሎማሲው ረገድ ከፍተኛ አስተዋፅዖ ያደረጉትንና ለነፃነት ትግላቸው ከፍተኛ ዋጋ የከፈሉትን ሁሉ ዋጋ የሚያሳጣ ውለታ ቢስ መሆንም ጭምር ነው፡፡ ሙሉውን ያንብቡ