ዴሞ ቅጽ፣ 39 ቁጥር 6: የኅብረተስብ እድገት፤ ቅራኔና ሂደትን መረዳት ያልቻሉ የሕዝብ አመጽና ፍንዳታ በጥቂት ተንኮለኞች ሴራ የሚመጣ ይመስላቸዋል። እነዚህ ሰዎች በአጼው ሥርዓት ላይ ጎርፍ እየመጣ ባለበት ጊዜ ችግሩን የፈጠሩትና የሚያባብሱት ጥቂት “በፈተና የወደቁ” የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ናቸው የሚለውን ክስ ሲደረድሩ ባጅተው ነበር:: የሚያሳዝነው ዛሬም ቢሆን የነበረውን ችግር ሁሉ — የኤርትራን ጉዳይ ሳይቀር — ያ ትውልድን ኢሕአፓ ፈጠረው ብለው አላዋቂነታቸውን የሚያጋልጡ አሉ። ሙሉውን ጽሑፍ ያንብቡ …