ከፍኖተ ዴሞክራሲ ወቅታዊ ሐተታ፡ የኢትዮጵያ ሕዝብ፤ ሁሉንም አይቶና ታዝቦ አሁን በአንድ አማራጭ ላይ ብቻ እንዲያተኩር ተገድዷል። ይኸውም፤ ወያኔ በመጨረሻው የመጥፊያ ዘመኑ፤ እስከዛሬ ሲቀብረው በኖረው የጥላቻ ቦምብ አማካኝነት፤ ሕዝቡን እርስ በርስ እንዳያፋጅና ሀገሪቱንም ወደ መጨረሻው አዘቅት እንዳይከታት፤ አስፈላጊውን ጥንቃቄ በማድረግ፤ ሀገሩን ከተቃጣባት አደጋ የመከላከል ኃላፊነት ያለበት መሆኑ ነው። ይህ ድምዳሜ ተስፋ የሚሰጥ ቢሆንም ቅሉ፤ ዕፎይታን የሚሰጥ ሊሆን ግን አይችልም። ለአያሌ ዘመናት በሠላም ተባበሮ፤ ተጋብቶና ተዛምዶ በአንድነት የኖረውን ሕዝብ፤ የውጭ መሰሪዎችና ሀገር-በቀል አጥፊዎች ሊያጠፉት እንደማይችሉ በታሪክ ተደጋግሞ የተመሰከር ክስተት በመሆኑ፤ ሁሉም ዜጋ ሊጽናና ቢችልም እንኳ፤ በሌሎች ሀገሮች ላይ የተከሰተው ዓይነት ጥፋት ሀገራችንን አያሰጋትም ብሎ መዘናጋት እንደማያስፈልግ፤ ስጋታቸውን የሚገልጹ የሀገርና የውጭ ሀገር የፖለቲካ ተንታኞች በርካታ ናቸው። ሙሉውን ጽሑፍ ያንብቡ ….