የኢሕአፓ ልሳን (ዴሞ ቅጽ 40፣ ቁ.8): በአጋጣሚም ይሁን ወይም የራሱ ዕጣ ፈንታ ሆኖበት እንደሆን በማይታወቅ ምክንያት፤ ከአለፉት ሰባ (70) ዓመታት ጀምሮ የሚፈራረቀው ወርሃ ግንቦት፤ ለሀገራችን የሚበጃት ወር አልሆነም። ምንችክ – ድርቅ ብሎ ሀገራችንን ለጥቃትና ለወረራ፤ ለጦርነትና ለጭቆና አገዛዝ የሚያጋልጣት ወር በመሆን ይታወቃል*-። ግንቦት ፤ ለኢትዮጵያ በተደጋጋሚ ችግር የሚያመጣባት ወር ሆኖ ቆይቷል። አሁንም ቢሆን፤ ግንቦት ወር፤ የሀገራችን ባላንጣ ወር መሆኑን ቀጥሎበታል። ለካ፤ በባህሉ፤ ሕዝቡ “አገመገመ ሚያዝያና ግንቦት ያለው ሊበላ፤ የሌለው ሊሞት!” እያለ የሚያጉረመርመው ወዶ አይደለም:: ሙሉውን ያንብቡ