በይልማ በጋሻዉ: የተከበረች የዉድ አገራችን ህልዉና በከባድ ጥያቄ ዉስጥ ስለመግባቱ የሚያጠራጥር አይደለም።ጭቆናን ስለመቃወምና ስለመታገል ረዥም የሚያኮራ ታሪክ ቢኖረንም ዛሬ ድሮ የነበረዉ ህብረትና ትብብር አይታይም። ይልቁንም ህብረት ማላላትና ግለኝነት ነዉ እያየለ የሚታየዉ። በጋምቤላ ላይ የዘር ማጥፋት ፋሺስታዊ እርምጃዎች ተወስደዋል። በኣማራ ህዝብ ላይ ገና ወደሥልጣን ከመጡበት ጊዜ ጀምሮ የዘር ማጥፋት ፋሺስታዊና አረመኔያዊ እርምጃዎች ተወስደዋል። በኦሮሞ ወገኖቻችን ላይ እንደዚሁ ተመሳሳይ ፋሺስታዊ እርምጃዎች ተወስደዋል። ለም መሬቶቻችንና ድንበራችን ጭምር ለዉጪ ኃይሎች እየተቸበቸቡ ናቸዉ። ሙሉውን ያንብቡ . . .