ዴሞክራሲያ: የኢሕአፓ ልሳን (ቅጽ 43፣ ቁ 1፣ መስከረም/ጥቅምት 2010 ዓ.ም) – . . . ያሉትን መለስተኛ ልዩነቶች ወደ ጎን በመተው ለሀገር ጠቃሚ የሆነ ኅብረት መመስረት ይገባል ብቻ ሳይሆን ይቻላልም። ይህ ግን ግለኝነትን አቸንፎ ሀገርን ማፍቀርና ማስቀደምን ይጠይቃል። ከሁሉም በላይ ኢትዮጵያ፤ ከሁሉም በፊት ሕዝባችን ካልን ሌሎች ጉዳዮች፤ የሀሳብና የአቋም ልዩነቶች ክብደታቸው ይቀንሳል። በሀገራችን ህልውና ላይ የተጋረጠውን አደጋ ከመጋተርና ከማስወገድ በፊት ሊቀድም የሚችል ምንም ግዳጅ የለም። አደጋውን ለማስወገድ መሳሪያ የሚሆነውን ኅብረት ከመመስረት የሚያግድ ምንም ጉዳይና ችግር ሊኖር አይችልም፤ አይገባም ማለት ነው። ኅብረቱ እውን ከሆነ የሽግግሩ ሂደትም ቀና አቅጣጫን ይዞ መጓዙ የማያቀር ነው። ተቃዋሚዎች ዓላማ የላቸውም፤ ተከፋፍለዋል፤ ወያኔ ከተወገደ ሕዝብ ያልቃል፤ ለመሆኑ ማን ወያኔን ሊተካ ይችላል የሚሉት ተስፋ አስቆራጭ አነጋገሮች ሁሉ ያከትማሉ ማለት ነው። ወያኔን አስወግዶ ሀገርን በፍትህና በዲሞክራሲ ለማስተዳደር–እንደ ወያኔ ለማጥፋት ለመበጥበጥ ሳይሆን–ችሎታውና ከዚያም በላይ ፍላጎቱ እንዳለን ሳናወላውል የተናገርነው ነው። ሙሉውን ያንብቡ