የኢትዮጵያ የፖለቲካ እስረኞች አንድነት ኮሚቴ (ሶሴፕ) የአሜሪካ ቅርንጫፍ፡ በካናዳ ዊኒፔግ የሰብዓዊ መብት ቤተመዘክር (ሙዚዬም) እ. ኤ. አ. ከ2008 ጀምሮ ሲታነጽ ቆይቶ የፊታችን ሴፕቴምበር 20 በከፍተኛ ድምቀት ለሕዝብ ዕይታ ክፍት ይሆናል፡፡ የካናዳ ሰብዓዊ መብት ቤተመዘክር ዋናው ዓላማው 1ኛ. ስለ ሰብዓዊ መብት ዕውቀትና ግንዛቤ ለማስጨበጥ፣ 2ኛ. ለሌላውም ወገን ከበሬታ ለማጎናጸፍና፣ 3ኛ. ውይይትን፣ ግንዛቤንና ተግባራዊነትን ለማበረታታ ነው፡፡ በዚህ ቤተመዘክር ውስጥ በዓለም ዙሪያ ስለሰብዓዊ መብት የተደረጉትን ታሪካዊ እንቅስቃሴዎችን ከሴፕቴምበር 20፣ 2014 ጀምሮ በቋሚነት ለሕዝብ ክፍት ያደርጋል፡፡ ሙሉውን ጽሑፍ ያንብቡ …