ኢሕአፓ፡ ሰሞኑን በኦሮሚያ ክልል የተለያዩ ከተሞች ውስጥ የወያኔ ባለስልጣኖችን የዘረፋ እቅድ በመቃወም ድምጻቸውን ባሰሙ ተማሪዎችና ሰላማዊ ዜጎች ላይ የወያኔ ወታደሮችና የጸጥታ ኃይሎች ተኩስ በመክፈት በርካታ ሰዎች መግደላቸውና ማቁሰላችው ታውቋል:: ኢሕአፓ በተፈጠረው ሁኔታ ሀዘን የተሰማው መሆኑን እየገለጸ ይህን አረመኒያዊ ድርጊት በጽኑ ያወግዛል:: ማናቸውንም ተቃውሞ በሰላማዊና በተገቢው መንገድ መግለጽ የዜጎች የማይገረሰስ መብት መሆኑ እየታወቀ ተቃውሟቸውን በሚያሰሙ ዜጎች ላይ ተኩስ ከፍቶ ፍጅት ማካሄድ የፋሽስቶችና የአምባገነኖች ባህርይ ስለሆነ ማናቸውም አገር ወዳድ ዜጋ ድርጊቱን ሊያወግዝና ሊኮንን ይገባዋል። ሙሉውን መግለጫ ያንብቡ …