ኢያሱ ዓለማየሁ: ከዕለታት አንድ ቀን ያኔ ድሮ ቦይንግ በሀገር ውስጥ በረራ ባልነበረበት ጠለፋ ኣካሂደን ነበርና አይዞህ በርታ ማሰማቱ ይገባል በሚል ነው ይችን አጭር መልዕክት የጻፍኩት። እኛም ጠላፊ ተብለን ታስረናል፤ ጠላፊ ተብለን የስደተኛ ወረቀት ተክልክለናል (አንዳንዶቻችን እስከ 1996 በፈረንጆች አቆጣጠር፤ በሀሰት ሰነድ መጓጓዝ ተገደናል) ወዘተ… ግን በወሰድነው እርምጃ ተጸጽተንም አናውቅም። ሀይለ መድህንም የመጣ ቢመጣ መቻልና መቋቋም አለበት። ዜጎች ደግሞ ዘመን ተቀይሮ በተለይ በባዕድ ሀገር መቃወምም የሚቻልበት ጊዜ ነውና ሊታደጉት፤ ሊከላከሉለት ያስፈልጋል። ከድሮ ጠላፊ ለኣዲስ ጠላፊ ያለኝ መልዕክት ምስጋናና አይዞህ በርታ ከጎንህ አለን የሚል ነው። ሙሉውን ጽሑፍ ያንብቡ...