ዜና ፍኖተ (የካቲት 30 ቀን 2008 ዓ. ም.): በትናንትናው ዕለት የተወሰኑ የአዲስ አበባ ዩነቨርስቲ ተማሪዎች በተለያዩ አካባቢዎች የወያኔ አግአዚው ጦር እያካሄደ የሚገኘውን ጭፍጨፋ በመቃወም የተቃውሞ ሰልፎች አደረጉ – ሰኞ ማታ በወለጋ ዩነቨርስቲ የአግአዚ ጦር በተማሪዎቹ መኖሪያ ክፍሎች በመሰማራት ከፍተኛ ድብደባ ማካሄዱና በዚህም በርካታ ተማሪዎች መጎዳታቸው ተዘግቧል። ደብደባው ጨለማን ተገን ያደረገ እንደነበር ሲታወቅ እስከአሁን በድብደባው ክፉኛ የተጎዱ 49 ተማሪዎች መኖራቸው ሲረጋገጥ በአንዳንድ ተማሪዎች ላይ የደረሰው ጉዳትም ለህይወት የሚያሰጋ ነው ተብሏል – የወያኔ ቡድን መሪዎች በኢትዮጵያውያን ላይ ያወጁትን ጦርነት በከተሞች ውስጥ በመግደልና በጅምላ በማሰር የአገዛዙን ዕድሜ ለማስረዘምና በስግብግብነት ኪሳቸውን ለመሙላት ጥረታቸውን በቀጠሉበት ሰዓት በገጠሪቱ ኢትዮጵያ የሚኖሩ ዜጎች ለዘመናት ከሚኖሩበት እያፈናቀሉ መሬታቸውን መቸብቸብ የተለመደ ሲሆን ከመሬታቸውን አንፈናቅልም ያሉትን ከፍጹም ሰብዓዊነት ውጭ ከመቶዎች ዓመታት በፊት አውሮፓውያን ፈንጋዎች የሚፈጽሙትን ዓይነት የጭካኔ ተግባር በደቡብ ኢትዮጵያ በኦሞ ሸለቆ በሶርማ ነገድ ላይ እየፈጸሙ መሆኑን ሰሞኑን በማኅበራዊ ገጾች ላይ የተለቀቀው ፎቶ አሳይቷል – በተመሳሳይ ዜና ባለፈው ቅዳሜ እንደተጀመረ የሚነገርለት በገለብ ሐመር ባኮ በኩራዝ ወረዳና በአካባቢው ከፍተኛ ፀረ-ወያኔ አመጽ እየተካሄደ መሆኑ ከስፍራው የተገኘ ዜና ያስረዳል፡፡ ሕዝቡ አካባቢውን አቋርጦ የሚሄደውን አውራ ጎና ቆፍሮ የተሸከርካሪ ትራንስፖርትን ሙሉ በሙሉ ማስተጓጎሉ ታውቋል፡፡ በአሁኑ ሰዓት የኢትዮጵያ ሕዝብ ከሰሜን እስከ ደቡብ፣ ከምስራቅ እስከ ምዕራብ፣ ከመሀል ሀገር እስከ ዳር አገር ወያኔን ለመደምሰስ እያመጸ መሆኑ የወያኔ ቁንጮዎች ክፉኛ እንደ ተረሸበሩ ለማወቅ ተችሏል – የታክሲ ሾፌሮች አድማ አድማሱን በማስፋት ባለፉት ቀናት በደብረ-ብርሀን፣ በደብረ-ሲና፣ በአጣዬና በካራቆሬ መቀጣጠሉ ታወቋል፡፡ ወደ እነዚህ ከተሞች የሚገባም ሆነ የሚወጣ ምንም ዓይነት የመንገደኛ ተሸከርካሪ እንደሌለ ለመረዳት ተችሏል – የወያኔ ቡድን መሪዎች የአንድ ዘር የበላይነት ያለውን ዘረኛና አምባገነን አገዛዝ ዕድሜ ለማስቀጠል ታማኛ አገልጋይ የፖሊስ ኃይል ዋና መሳሪያና ቀኝ እጅ መሆኑ የሚታወቅ ሲሆን ታማኝነታችው ያጠራጠረ የፖሊቲካ አመለካከታቸው ያልታወቀ ወይንም ዘራችው ካልተስማማችው ከሥራና ከሠራዊቱ በምክንያት ማባረር የተለመደ መሆኑ ይታወቃል – አጣዳፊ የተቅማጥና የትውከት በሽታ በአርባ ምንጭ ከተማ ውስጥ መከሰቱ ተሰምቷል። በሽታው በከተማዋ ውስጥ በሰፊው መሰራጨቱ ይሰማ እንጅ በበሽታው ሰብብ ህይወቱ ያለፈ ሰው ስለመኖሩ የተገለጸ ነገር የለም። የአርባ ምንጭ ከተማ የጤና ባለሙያዎች ግን በሽታው አደገኛና በቀላሉ በወረርሽኝ መልክ የሚስፋፋ በመሆኑ በአስቸኳይ ርብርብ መደረግ አለበት ይላሉ። ተጭነው ዝርዝር ዜና ያዳምጡ::