በስደት የኢትዮጵያ መምህራን ማህበር አባላት አስተባባሪ ኮሚቴ: . . . ተማሪዎች ገንዘባችውን፣ ጉልበታቸውንና ጊዜያቸውን ሰውተው ለፈተናው ተዘጋጀተው በመጠባበቅ ላይ እያሉ የሁሉም የትምህርት ዓይነቶች የፈተና ጥያቄዎችና መልሶቻቸው ፈተናው ከሚሰጥበት ከግንቦት 22 ቀን 2008ዓ.ም በፊት ባሉት ቀናት በፌስ ቡክ ላይ ተለቆ ለሕዝብ ይፋ ተደርጓል። ፈተናው መሰረቁና መልሶቹም በማህበራዊ ሚዲያ መሰራጨቱን ተማሪዎች የጧቱን ፈተና በመፈተን ላይ እያሉ የወያኔ የትምህርት ሚኒስቴር ፈተናው አልተሰረቀም በማለት መግለጫ ሰጠ። መግለጫውን በሰጠበት የሰዓታት ልዩነት ውስጥ ፈተናው መሰረቁን አምኖ ፈተናውን ሰረዘ። ወያኔና ቅጥፈት የማይለያዩ ሰውና ጥላ ናቸው፤ በአንድ አፍ ሁለት ምላስ ይሏል ይኼ ነው። ሙሉውን መግለጫ ያንብቡ