የርእሰ አድባራት ደብረ ሰላም ቅድስት ማርያም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ጊዜያዊ አመራር የሰላምና መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ

1ኛ. መንግሥት በዘርና በጎሣ ለ25 ዓመታት ህዝቡን ከፋፍሎ የገዛበት አመራር ለማንም ስላልበጀ ይህንንም ህዝቡ አውቆ ልዩነትን ወደ ጎን በመተው ወቀደመ አንድነቱ ተመልሶ በቁጣና በብሶት ለለውጥ በአንድነት ተነስቷል። መንግሥት የሀገሪቱን ሰላም ከፈለገ ማሠር መግደል ማቆም አለበት። እስከ አሁንም በማን አለብኝነት በንጹሀን ኢትዮጵያዊያን ላይ በከንቱ ያፈሰሰውን ደም አጥበቀን እናወግዛለን።

2ኛ. መንግሥት በአምባገነንነት በህዝባችን ላይ እየፈጸመ ያለውን ኢሰብአዊ ድርጊት እያወገዝን ህዝባችን ለሀገራችን የሚበጀውን መልካም አስተዳደር ለማምጣት የሚያደርገውን ብሄራዊ ትግል እንደግፋለን።

3ኛ. ቅዱስ ሲኖዶስ መንግሥት በህዝብ ላይ እየፈጸመ ያለውን ግፍ በይፋ እንዲቃወም እየጠየቅን ብፁዓን አባቶች፣ የገዳማት እና የአድባራት አስተዳዳሪዎች ግንባር ቀደም በመሆን በጎሣዎች መካከል ግጭት እንዲፈጠር መንግሥት የዘረጋውን የልዩነት ሥርዓት እንዲጠፋ ትውልዱን በማስተማር፣ በመምከርና በመገሰጽ ወደ ብሄራዊ አንድነት እንዲያመጡትና የህዝቡን ጥያቄ ጥያቄያቸው በማድረግ ከህዝቡ ጎን እንዲቆሙ እንጠይቃለን። ሙሉውን መግለጫ ያንብቡ ….
nbsp;