ከስቶክሆልም የተላከ: ለዚህ ፅሑፍ ዕለተ ትንሣኤ! የሚል ርዕስ መስጠት የፈለግሁት ካለምክንያት አይደለም። አንድ ቀን ኃይሉን ለመጠየቅ ቤቱ ሄጄ፣ ‘’እንደምን ሰንብተሃል? ጤንነትህስ እንዴት ነው?’’ ስለው ከሰጠኝ መልስ በመነሳት ነው። “ደህና ነኝ! ሰው እኮ በህይወት እስካለ የሚቻለውን መልካም የሆነን ነገር ሁሉ እያረገ ከኖረ፣ ሞት መፈራት የለበትም፣ ይህማ ህልፈተ ሥጋ ነው። ትንሣዔውማ ገና ነው። በሥጋ ካለፈ በኋላም የሚቀጥል እስከዚያ እለትም ብዙ የሚያደክም፣ የድምር ሂሳብ መክፈያ፣ የሥራና የተግባር ውጤት ነው’’ አለኝ። አልገባኝም አብራራልኝ ብለውም፣ ያ ሁሌ ፊቴ ድቅን የሚለውን ፈገግታውን እያሳየኝ፣ አማርኛውን ከግዕዝ እያቆላለፈና እያስተሳሰረ ስላከበደብኝ፣ ይህን መሰል ውስጠ ወይራ ጣዕም ያለውን ጨዋታውን አቋርጬው ሌላ ጨዋታ ውስጥ ገባን። ሙሉውን ያንብቡ