ዴሞክራሲያ: የኢሕአፓ ልሳን (ቅጽ 43 ቁ.3 ጥር/የካቲት 2010) – ወርሃ የካቲት ከዛሬ 102 ዓመት በፊት አባቶቻችን በጣሊያን ቅኝ ገዥና ወራሪ ኃይል ላይ የተቀዳጁትንና የጥቁር ሕዝብ የጀግነነት ተምሳሌት የሆነውን የአድዋን ድል በከፍተኛ ኩራትና ወኔ የምናከብርበት እንዲሁም የካቲት 23 በግራዚያኒ የተጨፈጨፉ ሰማዕታት ወገኖቻችንን በሀዘን
የምናስታውስበት ወር ቢሆንም የዛሬ አርባ አራት ዓመት በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ ድምቀትና ታላቅነት የተቀዳጀውን የ1966ቱ ሕዝባዊ አብዮት በአድናቆት የምንዘክርበት ወር ነው። ይህን አብዮት ምን አመጣው? እንዴት ተከሰተ? ማን ማን ተሳተፈበት? ማንስ ላይ አነጣጠረ? በአብዮቱ ሕዝቡ የአነሳቸው ጥያቄዎች ምን ነበሩ? እንዴትስ ተስተናገዱ? በሂደቱ ምን ምን ተከሰተ? እንቅስቃሴውስ ወደፊት ገፋ ወይስ ተደናቀፈ? …ወዘተ የሚሉት ጉዳዮች በዝርዝርና በስፋት በየጊዜው የተዘገቡ መሆናቸው ይታወቃል። ሙሉውን እትም ያንብቡ