ከቤልጅግ አሊ፡ በክፍል አንድ በመኪና ተጠቅጥቀን ወደ ቀበሌ 07 እንደተሰወድን ገልጬ ነበር ያቆምኩት። በከርቸሌ የነበርነው የልደታ ልጆች ወደ ከፍተኛ 22 ቀበሌ 07 እንድንወሰድ መወሰኑን ሲነገረን ሁላችንም የሕይወታችንን የመጨረሻው ጉዞ እንደጀመርን ነበር የተሰማን። የምናውቀው ጉዳይ ቢኖር ከመካከላችን አንዳንዶቻችን እንደምንገደል ነው። ምንአልባትም ሁላችንም እንሞት ይሆናል። ሞት ቀላል ነው። አንዳንድ ሰዎች መሞት ቆራጥነትን ይጠይቃል ሲሉ ይገርሙኛል። ለእኔ በዛ ወቅት ከባድ የነበረው በበዚህ ፍትህ በጎደለበት፣ አረመኔዎች በነገሱበት፣ እርጉዝ ከነልጇ በተገደለችበት፣ እናት የልጇን አስክሬን እንዳታነሳ በተከለከለችበት፣ የሰው ስጋ በእሳት በተቃጠለበት… ሙሉውን ጽሑፍ ያንብቡ…