ዴሞ (ቅጽ 43 ቁ.4 መጋቢት/ሚያዚያ 2010 ዓ.ም) : ከአለፉት ጥቂት ዓመታት ወዲህ ዘረኛውንና አምባገነኑን የወያኔ አገዛዝ ለማስወገድ፤ ብርቱ መሥዋዕትን ያስከፈለ ሕዝባዊ ዐመፅ ተካሄዷል። በተለያዩ አካባቢዎችና በልዩ ልዩ የኅብረተሰብ ክፍሎች ጠበብ ያሉ ጥያቄዎችን በማንሳት የተጀመረው ሕዝባዊ የተቃውሞ እንቅስቃሴ በሂደት አድማሱን አስፍቶና በርካታ ታጋዮችን አካትቶ የትግሉን ዒላማ አገዛዙን ወደ ማስወገድና ሥርዓቱን ወደ መለወጥ አሳድጎ የሞት የሽረት ግብ ግብ በማካሄድ ላይ ይገኛል። የትግሉ ግብ ገና ከዳር ባይደርስም በየአካባቢው የተካሂዱት ሕዝባዊ እንቅስቃሴዎች፣ አድማዎችና ዐመጾች አገዛዙን አሽመድምደውታል፤ አከርካሪውን መትተው አዳክመውታል፤ በትዕቢት የተወጠረውን ቡድን በተከላካይ ድባብ እንዲሸበብ አድርገውታል። በየጊዜው እያደገ በመጣው ሕዝባዊ እንቅስቃሴ ምክንያት ገዥው ክፍል በውስጥ መከፋፈልና መሰንጠቅ ደርሶበታል፤ ያልተቋረጠ ግምገማ እንዲያካሄድ ተገድዷል፤ ጥፋተኛ ነን ብሎ በይፋ ወንጀሉን ለመናዘዝ በቅቷል። ሙሉውን ጽሁፍ ያንብቡ . . .