በፍኖተ ዴሞክራሲ የኢትዮጵያ አንድነት ድምጽ: ሰሞኑን፤ በሰሜናዊው የሀገራችን ፤ ክፍል በሆነው ጎንደር፤ የተቀጣጠለው ትግል ፤ በመላው የሀገሪቱ ፤ግዛት ከሚካሄደው ሀገራዊ ትግል ጋር፤ አንድ አካል-አንድ አምሳል ሆኖ ቀጥሏል ። የጎንደርን ሕዝብ ቅስም ለመስበር የታቀደው የወያኔ ጠላትነትም ሕዝቡን ሊበግረው – ሊያስበረግገው እንዳልቻለ አስመስክሯል ። ምናልባት ፤ ሊዘገይ ይችል ይሆናል እንጅ፤ ፍርድና በደል፤ በፍትኅ ሸንጎ ፤ ዐይን ለዐይን የሚተያዩበት ቀን ሩቅ አይሆንም። የፍትኅ ሸንጎ፤ የራሱን ጊዜ ጥብቆ ይመጣል። በተበደሉት ወገን ቆሞ፤ ለተገፉት፤ ለተበደሉት ፍርዱን ይሰጣል። ኢትዮጵያ፤ ዘለዓለም ፍርድ የጎደለባት ፤ፍትኅ- ርትዕ ደብዛው የጠፋባት ፤ ምድራዊ – ሲዖል፤ ሀገረ- ጉግ-ማንጉግ ሆና አትቀርም ።
በጎንደር የተነሳው ሕዝባዊ አመፅ፤ እንደ አኩሽታራ (የእሬት ስር) የጠፋ መስሎ፤ነገር ግን ውስጥ -ውስጡን የሚቀጣጠል ዕሳት ነው። እንደ ቋያ/ መንጠር ዕሳት፤ እየተየያዘ ፤ እየተቀጣጠለ ፤ እየለበለበ ፤ እየፈጀ፤ እያቃጠለ፤ እያኮማተረ እያንገበገበ፤ እያወደመ መሄዱን ይቀጥላል። ዋ ! ይብላኝ ለግፈኞች ። እግዚኦ! ለሀገር ጠላቶች! ለፍርድ ሸንጎ መቅረባቸው አይቀርምና! ሙሉውን ያንብቡ