ፍካሬ ዜና ከፍኖተ ዴሞክራሲ የኢትዮጵያ አንድነት ድምጽ ሬዲዮ (ጥቅምት 136 ቀን 2009 ዓ.ም.) – ሻዕቢያ ወያኔን የሚተካው ህዝባዊ መንግስት ወደቦችን ያስመልሳል የሚል ስጋት ያለው መሆኑ ታወቀ – ንብረታቸው የወደሙባቸው አንዳንድ ክፍሎች ድርጅቶቻቸቸው ከቀረጥ ነጻ እንዲሆኑ ጠየቁ – አስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ወያኔን እየጎዳ ነው ተባለ – የወያኔ አገዛዝ ወታደሮቹን ሂራን ከተባለው የሶማሊያ ግዛት አስወጣ – በአስውትራሊያ ፐርዝ ከተማ ኢትዮጵያውያን የተቃውሞ ሰልፍ አደረጉ።
ሻዕቢያ ወያኔን የሚተካው ህዝባዊ መንግስት ወደቦችን ያስመልሳል የሚ ስጋት ያለው መሆኑ ታወቀ
የኢትዮጵያ ሕዝብ ትግል ያስደነገጣቸውና ሊያደናቅፉት ጥረት ለጀመሩት ስምሪታቸው ጎጂ እንጂ የሚጠቅማቸው አለመሆኑ ተነግሮአቸዋል ተባለ። “ሳትነግሩን አማራውና ኢሕአፓ እጃችን ላይ ፈነዱብን!” በሚል በቦታው ያሉትን ኢትዮጵያዊ ተቃዋሚ ቡድኖች በወቀሰ አብጠለጠለ የሚባልለት ሻዕቢያ ነጻ ኢትዮጵያ ወደቦችን ለማስመለስ ውጊያ ተገጥገጥመናላች በሚል አሉታዊ እርምጃ ለመወሰድ ከተነሳ ይጎድዋል እንጂ አይጠቅመውም ተብሎ እንድተነገረው ለማወቅ ተችሏል። ነጻ ኢትዮጵያ ችግሮችን ለመፍታት ዋና መንገዷና መሳሪያዋ ድርድር ይሆናል እንጂ ጦርነት አይሆንም ያሉ ገምጋሚዎች ሻዕቢያን ማስደንገጥ ይጠቅመናል ያሉ ክፍሎች የሚያሰሙትን ቡታ ማክሸፍ ያስፈለግል ብለዋል። ተመሳሳይ ገለጻና ማሳሰቢያ ለጎረቤት ሱዳንና ለግብጽም ለአሜሪካና ለአውሮፓ ሀገሮችም መሰጠቱትም ተዘግቧል። ሕዝብ ድምጹ ባልተሰማበት፣ ጆሮን ለመጥለፍና አቅዋም ለማስቀየር የተቻለውንና አስፈላጊ የተባለውን እርምጃ መውሰዱ ግን ተገቢ ነው ያሉት እነዚሁ ታዛቢዎች የኢትዮጵያን ሕዝብ ትግል መደገፉ ይበልጥ የተሻለና የሚያዋጣም ነው ሲሉ ጠቁመዋል።
ንብረታቸው የወደመባቸው አንዳንድ ክፍሎች ድርጅቶቻቸው ከቀረጥ ነጻ እንዲሆኑ ጠየቁ
በኢትዮጵያ በተለያዩ አካባቢዎች በሕዝባዊ አመጾች ጉዳት የደረሰባቸው ኩባንያዎችና የግል ባለሀብቶች በንብረቶቻቸው ላይ የደረሰውን ኪሳራ ለመሸፈን ከአገዛዙ ካሳ ጠይቀው የተፈቀደላቸው መሆኑ ታውቋል። አብዛኞች ካሳ እንዲከፈላቸው የተደረገው ከአገዛዙ ጋር ቅርበት ያላቸው ወይም ከአንድ ብሔረሰብ የመጡ ባለሀብቶች መሆናቸውም ታውቋል። የአላሙዲ ንብረት የሆነው የደርባ ሲምንቶ ፋብሪካ እና የዳንገቴ ሲምንቶ ፋብሪካ በርካታ ንብረት የወደመባቸውን ለማካካስ ስራቸው ከቀረጥ ነጻ የሚሆንበት ሁኔታ እንዲመቻች ጠይቀዋል። የአላሙዲው ደርባ ሲምንቶ 54 ከባድ መኪናዎች የወደሙበት ሲሆን የዳንገቴው ሲምንቶ ፋብሪካም ከ30 ሚሊዮን ብር በላይ ንብረት እንደወደመበት ተነግሯል። የወያኔ አገዛዝ በዚህ ላይ ምን ውሳኔ እንደሚሰጥ አልታወቀም።
አስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ወያኔን እየጎዳ ነው ተባለ
ወያኔ ያወጀው ያስቸኳይ ግዜ አዋጅ ተመልሶ የራሱን ወንበዴ አገዛዝ እየጎዳ እንጂ ከሕዝብ አንጻር ያመጣው አዲስ ነገር የለም ሲሉ የፖለቲካ ተንታኞች ደምድመዋል ተባለ ። የኢንተርኔት መቋረጥ እንዲሁ ጉዳቱ በአብላጫው ለወያኔ መሆኑ ተረጋግጧል ። ይህ በሁለት አሃዝ አደገ ተብሎ የሚዋሽለት የወያኔ የከሰረ ኢኮኖሚ የባስ ቀውስ ውስጥ እየገባ መሆኑም በመነገር ላይ ነው ። የኑሮ ውድነት ብለው ሁኔታ ይባባሳል እንጂ አይቀንስምም ተብሏል ። ወያኔ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ያወጀው በራሱ ነው ብለው የተቹ ክፍሎች በዚህም በዚያ የወያኔ ዕድሜ አጭር መሆኑን ሊቀይረ አይችልም ብለዋል።
ወያኔ ወታደሮቹን ሂራን ከተባለው የሶማሊያ ግዛት አስወጣ
የወያኔ አገዛዝ ወታደሮቹን ሂራን ከተባለው የሶማሊያ ግዛት ያስወጣ መሆኑን በአካባቢው ከሚገኙ የአይን እማኞች ለማወቅ ተችሏል። ከጥቂት ቀናት በፊት በወያኔ ወታደሮችና በአልሸባብ መካከል በአካባቢው ውጊያዎች መኖራቸው የተዘገበ ሲሆን ቦታው አሁን በአልሸባብ ቁጥጥር ስር መዋሉ ተረጋግጧል። በወያኔ ወታደሮች መካከል የእርስ በርስ የተኩስ ልውውጥ እንደነበር ተሰምቷል። በሕዝባዊ ተቃውሞ እና በተከተለው አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ምክንያት በወያኔ ወታደሮች ውስጥ ውጥረትና ያለመተማመን ያለ መሆኑ እየተነገረ ሲሆን የተኩሱ ልውውጥ የዚህ ነጸብራቅ ይሁን አይሁን የታወቀ ነገር የለም።
በአስውትራሊያ ፐርዝ ከተማ ኢትዮጵያውያን የተቃሞ ሰልፍ አደረጉ
በምዕራብ አውስትራሊያ በፐርዝ ከተማ ከተለያዩ ብሔረሰቦች የተውጣጡ ኢትዮጵያውያን የወያኔ አገዛዝ እያካሄደ ያለውን ጭፍጨፋ በማውገዘ ሰላማዊ ሰልፍ አካሄደዋል። ሰልፈኞቹ የወያኔ አገዛዝ የሚፈጸመውን ግፍ በማወገዝ የተለያዩ መፈክሮች ያሰሙ ሲሆን የአውስትራሊያ መንግስት ለዚህ አርመኔያው አገዛዝ የሚያደርገውን እርዳታና ትብብር እንዲያቆም ጠይቀዋል።