ከጳጉሜን 2006 ዓ.ም ጀምሮ ጋምቤላ ክልል፣ መዠንገር ዞን፤ ጎደሬ ወረዳ በተለይ ሜቲ ከተማ ውስጥ ግድያና በአካባቢውም ግጭቶች መካሄዳቸውን የተለያዩ የዜና ምንጮች እየዘገቡ ናቸው። ከ500 በላይ ሰላማዊ ሰዎች ተገለዋል፤ ብዛታቸው በውል ያልታወቀ ደግሞ ለከባድ የመቁሰል አደጋ ተጋልጠዋል። «ግጭቱ የሚካሄደው በአማሮች ላይ ነው» የሚለው መኢአድ ባወጣው መግለጫ መሠረት፣ የመንግሥት ካድሬዎችና ፌዴራል ወታደሮች እጃቸው እንዳለበት አመልክቷል። የአሜሪካ ድምጽ ሬዲዮ ከድርጅቱ አመራር አካል እና የዓይን ምስክር ከሆኑ ጉዳተኞች ጋር ያደረገውን ቃለ-ምልልስ ያዳምጡ።