(በፍኖተ ዴሞክራሲ የኢትዮጵያ አንድነት ድምፅ) – ሀገርና ሕዝብ፤ አንድም ሁለትም ናቸው። አንዱን ከሌላው ለይቶ ማየት ያስቸግራል። በብዙ ሀብሎች የተሳሰሩ፤ የተዋኻዱ ናቸውና! ያንዱ አለመኖር፤የሌላውን አለመኖርን ያስከትላል። ሀገር ማለት፤ መሬቱና አፈሩ፤ ጋራና ሸንተረሩ፤ ወንዙና ባህሩ፤ ብቻ የሚመስላቸው ይኖሩ ይሆናል። ይኽ አባባል ግን ብቻውን፤ ሀገርን ለመግለጽ በቂ ሊሆን አይችልም፡፡ ያ ቢሆንማ ኖሮ ፤ እንደ ሳሃራ፤ ካላሃሪና ጎቢ የመሳሰሉ ምድረ-በዳ (በረሃዎች ) እንደ ሀገር በተቆጠሩ ነበር! ሕዝብ ስለማይኖርባቸው የሀገርን መስፈርት ሊያሟሉ አልቻሉም። ሀገርን፤ ሀገር ብሎ ለመጥራት፤ በግድ ነዋሪ ሕዝብ መኖር አለበት! አምጡ-ደገሙ ቢባል ሕዝብን የሚተካ አንዳችም ነገር አይኖርም። ሙሉውን ጽሁፍ ያንብቡ