ከዚህ ዓለም በሞት የተለየችበት የ80ኛ ቀን መታሰቢያዋ ሲከበር ለኢሕአፓ አባላት እናት፣ እህትና ጓድ የነበረችውንና እንዲሁም ኢሕአፓ እያካሄደ ባለው ሕዝባዊ ትግል ግምባር ቀደም ደጋፊ፣ ተባባሪና ተሳታፊ በመሆን ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያበረከተችውን ጀግናዋን አርቲስት ጠለላ ከበደን በአንክሮ እናስታውሳታለን። ከሙያዋ ጎን ለጎን ለኢትዮጵያ ሉዓላዊነት እንዲሁም ለሕዝቧ መብትና አንድነት በተደረጉ ትግሎች ውስጥ አኩሪ አስተዋጽኦ ያደረገችው ጠለላ ከበደ በአገራችን ታሪክ ውስጥ ጎላ ያለ ቦታ ያላት ናት። . . .
የአርቲስት ጠለላ ከበደ ተሳትፎ ሁለ ገብ ነበር። በአካል ተገኝቶ መሥራት በሚያስፈልገበት ቦታ ላይ ጉልበቷን ሳትቆጥብ በመሳተፍ፣ የገንዘብ አስተዋጽኦ በሚያስፈልገው ሥራ ላይ የራሷን ገንዘብ በመለገስና ሌሎች አስተዋጽኦ እንዲያደርጉ በመገፋፋት፣ ለትግል አጋሮቿ ምክር በመስጠትና ተመክሮ በማስተላለፍ፣ እንዲሁም በሙያዋ ጣዕመ ዜማዋዎችን በማሰማት ታጋዮችን ስታበረታታ ቆይታለች። የኢሕአፓ ምሥረታን ለማስታወስ በዋሽንግተን ዲሲ በተዘጋጁ በዓሎች፣ የገንዘብ ማሰባሰቢያ ምሽቶች፣ እና ሕዝባዊ መድረኮች ግምባር ቀደም አደራጅና ተሳታፊ የነበረች ሲሆን በአሜሪካ የተለያዩ ከተሞችም በስፖርት ፌዴሬሽን በተዘጋጁ በዓሎች ላይ በመገኘት አስተዋጾ አድርጋለች። ሙሉውን መግለጫ ያንብቡ . . .