ደቂቀ ገሞራ፡ ገሞራው በበረከተ መርገም ባነሳቸው ጭብጦች ጠቅለል ተደርገው ሲታዩ የሰው ልጅ በእድገቱ፣ በሥልጣኔው የፈለሰፋቸው ቁሶችና የፈለሰማቸው ይትበሀሎች ለሰው ልጅ ጠቀሜታነት መዋላቸው ቀርቶ ለሰው ልጅ ጥፋትና ውድመት መዋላቸውንና ይህን እኩይ ድርጊት አስፈጻሚና ፈጻሚዎችን ኮነነ፡፡ እረገመ፡፡ ውጉዝ ከመ አርዮስ አላቸው፡፡ እንደ አርዮስ ይለዩ ይረገሙ፡፡ ዝነኛው፣ አንጋፋው ዘፋኝ ዓለማየሁ እሸቴ ያቀነቀነው ፀረ- ኮሎኒያሊዝም የሆነው ያ ጥቁር ግሥላ የተሰኘው ግጥም የደብተራው የጸገየ ወይን ነው፡፡ ስንኞቹ የጸገየ ወይንን የመጠቀ ቅኔ ዘራፊነት ይመሰክራሉ፡፡ በረከተ መርገም ዛሬም ድምጹ በቅኔው ማህሌት በተዘረፈበት ዘመን ሳይቀነበብ የዛሬው ግፈኛ፣ ዘራፊ፣ ዘረኛና ደም አፍሳሽ የሆነው ወያኔንም ከነግፉ ከነግሳግሱ ነፋሪት ያንፍርህ ይለዋል፡፡ ሙሉውን ሐተታ ያንብቡ …