ወጣቱ ዛሬም ለሀገሩና ለወገኑ ቤዛ ነው


(ዴሞ ቅጽ 46 ቁ. 2) . . . ከራሱ ከወያኔ ማህፀን የወጣውና ሁለተኛ ዙር የብሔር ፅንፈኝነትን ያስቀጠለው የኮሎኔሉ አገዛዝ የመቀሌው አውሬ ለሥልጣኑ መሰናክል እየሆነ ሲመጣና በአማራው ላይ ለተፈፀመው እልቂት ማዘናጊያም ይሁን በሌላ ምክንያት ተገፋፍቶ፣ ከኢትዮጵያ ጠላቶች አንዱ -ወያኔ- መመታቱ እሰዬው የሚያሰኝ ነው፡፡ ሆኖም ስብሃትን አስወግዶ በቦታው ከሻዕብያው ቁንጮ መመሪያ መቀበል፣ በኢትዮጵያ ጉዳይ ጣልቃ ገብቶ ዳግም ሀገር እንዲዘርፍና በሕዝብ ላይ የአፈና ወንጀል እንዲያሰፋ መጋበዙ፣ ለኮሎኔሉ ገሀድ የወጣ ፀረ-ኢትዮጵያዊነት ተጨማሪ ማስረጃ ነው፡፡

አማራው ደም ከፍሎ ያስመለሰውን መሬቱን ዳግም ለመንጠቅም ከብልጽግናዎቹ የሚደመጥ ሹክሹክታ ያለፈ እንደሚሆን ብዙ ሳይቆይ የሚጋለጥ ነው የሚሆነው፡፡ እስከ 80 የሚደርሱ ቋንቋዎች በሚነገሩባት አገር፣ አንድ ጎሳ በበላይነት እንዲገዛ ለማድረግ ከዕቅድ አልፎ ተቋም እየገነባ ሲሆን፣ በዛው ልክ ታሪኳንና ሕብረ ብሔራዊ እሴቶቿን ቀስ በቀስ በማፍረስ ላይ ይገኛል፡፡ ይህን ሁሉ ሲያደርግ ኢትዮጵያን አንድ ለማድረግ፤ ኢትዮጵያ እንዳትፈርስ፤ ለኢትዮጵያ አንድነት ሲባል፣ … ነው ሕገመንግሥቱን የማንቀይረው በሚል የማይቀባጥረው፣ነገር የለም፡፡ የሚያሳዝነውና ከንቱ አሽቃባጭም ስለበዛ የልብ ልብ ተሰምቶት ሊሆን ይችላል፣ ይህ ዓይን ያወጣ ሸፍጡ ከመደጋገሙ የተነሳ የሕዝብ ጆሮም ማዳመጡን እያቆመ የመጣ ይመስላል፡፡ . . . እዚህ ላይ በመጫን ሙሉውን ጽሁፍ ያንብቡ