በስደት የኢትዮጵያ መምህራን ማህበር አባላት አስተባባሪ ኮሚቴ – የኢትዮጵያ መምህራን ጎሳን መሰረት ባደረገው በወያኔ ዘረኛ ስርዓት ላለፉት 26 ዓመታት በእጅጉ ተጠቂ እንደሆኑ ይታወቃል። መምህራን ወያኔ በሰፋው የጎሳ ኮሮጆ ውስጥ ለመግባት ፍቃደኞች ስላልሆኑ ብቻ ለእኩል የትምህርት ደረጃ እኩል ክፍያ፣ የትምህርት እድል ፣ የደመወዝ ጭማሪ፣ ወ.ዘ.ተ ሲነፈጉ ኖረዋል። ወያኔ በየዓመቱ መጀመሪያ ላይና በተለየዩያ ጊዜያት በትምህርት ስም የፖለቲካ ስራውን ለማካሄድ በሚያዘጋጃቸው ስብሰባዎች ላይ መምህራን የተለያዩ ሕጋዊ የመብት ጥያቄዎችን በማቅረባቸው ብቻ ተገድለዋል፣ ታሰረዋል፣ ከስራ ተፈናቅለዋል፣ የግዴታ ዝውውር ተፍጽሞባቸዋል፣ ለስደት ተደርገዋል፣ የወያኔ ዘረኛ ስርዓት ሰለባ ሆነው በገዛ አገራቸው እንድሁለተኛ ዜጋ ሊቆጠሩ በቅተዋል።ይህ በመምህራን ላይ የሚፈጸመው ዘርፈ ብዙ የግፍ ቀንበር ሊወርድ ካለበት ጊዜው ነገ ሳይሆን ዛሬ ነው። መምህራንም ሆኑ ሌሎች ሲቢክ ማህበራት ያነሷቸው የመብት ጥያቄዎች ምላሽ የሚያገኙት የወያኔ ዘረኛና ገዳይ ስርዓት ተገርስሶ በምትኩ ሕዝባዊ ሥርዓት ሲቋቋም ብቻ ነው። ሙሉውን መግለጫ ያንብቡ