ዴሞክራሲያ (የኢሕአፓ ልሳን: ልዩ ዕትም፣ ነሐሴ 2010 ዓ.ም.)- የሀገራችን ተጨባጭ ሁኔታ ለደግም ይሁን ለክፉ ለውጥን ሲያሳይ ቆም ብለን፤ አደብ ገዝተን የት ደርሰናል ብለን መመርመር ግዴታችን ሆኖ ይገኛል። በተለይም ግርግርና ውዥንብር ሲሰፍን ከሀይ ሃይታው ፈንጠር ብሎ በጥሞና ምን እየተካሄደ ነው? ወደ የትስ እያመራን ነው? ብለን ስናጤን ምን ማድረግ እንዳለብን ግልጽ ሆኖ ይከሰታል። ታሪክ የረሳ ስህተትን ይደግማል ነውናም በተደጋጋሚ የትግላችንን ድል እየተቀማን ህዝብም ለመከራ ኢትዮጵያም ለጥፋት ስትዳረግ አይተናልና ዛሬ ሀገር አድኑን ትግል አደናቅፈው ለከፋ አደጋና የርስ በርስ ፍጅት ሊዳርጓት የተነሱትን በጊዜ መቋቋም መቻልና ሀገራችንን መጠበቅ እንዳለብን ግልጽ ነው። ዛሬ ከመቸውም ጊዜ በበለጠ ኢትዮጵያ በክፉ አደጋ ላይ ናት። ሙሉውን እትም ያንብቡ. . .