በፍኖተ ዴሞክራሲ የኢትዮጵያ አንድነት ራዲዮ: ዛሬ የኢትዮጵያ ሕዝብ ፤ያገር ያለህ ! የዳኛ ያለህ ! የህግ ያለህ! የመንግሥት ያለህ ! እያለ ይጮኻል። ሀገርም፤ ዳኛም፤ መንግሥትም እንደሌለው ልቡ እያወቀው፤ ጩኸቱን የሚሰማለት አገኛለሁ ብሎ ግን ዕሪታውን ቀጥሏል። ሀገርና ሕዝብ አኩርፈዋል። ተቀይመዋል። ተቀያይመዋል። ተሸሽገዋል። ተደብቀዋል። መላ-ቅጡ ጠፍቷቸዋል። ቅስማቸው ተሰብሮ፤ አንገታቸውን ደፍተዋል። ሰማይ -ምድሩም ተደፍቶባቸዋል። እርስ- በእርሳቸው እንዳይወያዩ፤ እንዳይመካከሩ፤ ፊት ተዘዋውረዋል። ተኮራርፈዋል። የጋራ መንግሥትና ህግ፤ ዳኛና ፍትኅ-ርትዕ በመጣታቸው፤ በአውላላ ሜዳ ላይ ይማልላሉ። ይዋልላሉ። አቃፊ-ሰብሳቢ መንግሥት አጥተው፤ በበታኝ ሥርዓት፤ ተበታትነዋል። ከሀገራቸው ዕትብት ጋር እንዲቆራረጡ እየተደረጉ ነው። ሀገራቸውም፤ ስሟ ብቻ እንጅ፤ ጨገሬታዋ እንደለለ ተቆጥሯል። ኢትዮጵያና ሕዝቧ ጮኸታቸውን የሚያዳምጥላቸው ታዛቢ አላገኙም። ሙሉውን ያንብቡ