(የፍኖተ ዴሞክራሲ የኢትዮጵያ አንድነት ድምጽ ሐተታ): በምጥ ላይ ያለች እንጅ፤ ማርገዟን ማንም ያላወቀላት ሀገር በመሆኗ፤ ኢትዮጵያ ዛሬ፤ “ፈጣሪ በደህና ያገለግልሽ” የሚላት፤ አንድ ዘመድ-ወዳጅ እንኳን አላገኘችም። ተቆርቋሪዋ ነን ባዮችም ቢሆኑ፤ የአራስ ገንፎ ለመብላት ከማቋመጥ አልፈው፤ እንዴት በሠላም እንደምትገለገል እንኳን ብልሃቱ ተሰውሮባቸዋል። ቅጥ-አምባሩም ጠፍቶባቸዋል። ምጧ ተግባድዶ በሠላም የምትገላገልበትን መፍተሄ በጋራ ለመግኘት አልቻሉም። ሞክረውም ከሆነ እንካሁን አልተሳካላቸውም። ሙሉውን ሀተታ ያንብቡ