ቢንያም ግዛው (ኖርዌይ ኦስሎ): ይታደሉታል እንጂ አይታገሉትም ተብለን እድላችንን ስንጠብቅ ብዙ ቆየን። በርካታ ቋንቋ የሚወራባት ሀገራችን በተረትና ምሳሊያዊ ንግግር ሀብታም በመሆንዋ ብዙዎች ሀሳባቸውን በተለያየ መንገድ እየገለጹ ይግባባሉ። ይግባባሉ። አሁን ግን የማይፈቱ ህልሞች፣ ፍቺ ያልተገኘላቸው ተረቶች እና ቅኔዎች መስማት ከጀመርን ሁለት አስርት አመታት አልፈው ሦሥተኛው አጋማሽ ላይ ደርሰናል። በሀገራችን ኢትዮጵያ የሕዝብን ምላሽ የሚጠብቁ በየቀኑ ተፈብርከው ፈቺ ያጡ ብዙ እንቆቅልሾች እና ፈሊጦች ፈሊጦች ለጆሮ አታክተዋል። ወያኔ ህዝቡን እንደ ሁለተኛ ዜጋ ቆጥሮ ነዋሪው በፍርሀት እና በስጋት እንዲኖር አድርጎ አፋኝ እና ጨቋኝ ስርዐት ካነገሰበት ጊዜ አንስቶ እንኳን በቀለማችን እና በደማችን በደማችን ብቻ መግባባት ይቅርና በአንድ ቋንቋ እየተነጋገርን በሁሉም ዘርፍ አለመደማመጡ እና ግርግሩ ተባብሷል። ሙሉውን ያንብቡ