Hailu Bitanya: እኔ እንደሚመስለኝ አቶ አሰፋ ጫቦ የራሱ መፅሃፍ ምረቃ ላይ በእውቀቱ ስዩም ጠየቀኝ የሚለው የኢጫት ሊቀመንበርነት ጥያቄ ምቾት የሰጠው አይመስለኝም። ከዛም ባሻገር አቶ አሰፋ በተለያየ ፅሁፉና ቃለምልልሱ ለራሱ የሚሰጠውን እጅግ የተጋነነ ግምትና ሌሎቹን ለመወንጀል የሚሄድበትን ረጅም ርቀት አንብቤና አዳምጨ አቶ አሰፋን መታዘቤ አልቀረም።
አቶ አሰፋ ጫቦ ብዙ ጊዜ ባልተረጋገጠና ለእሱ ብቻ በሚታወቅና ሌሎች በማያሳምን የሞቱትንም በህይወት ያሉትንም ታላላቅ ሰዎች ሲወቅስ መስማት የተለመደ ነው። ፕሮፌሰር አስራትን ወልደየስን፣ ባሮ ቱምሳን፣ ተስፋየ ደበሳይን፣ ብርሃነመስቀል ረዳን፣ ዘሩ ክህሽንን፣ ፊታውራሪ መኮንን ዶሪን፣ ንግስት አዳነንን ፣ሃይሌ ፊዳን .. ከብዛታቸው የተነሳ እዚህ ለመጥቀስ የሚያስቸግሩ ብዙ ሰዎችን በአገኘው አጋጣሚ በፅሁፎቹም በቃለምልልስም ሲወቅስና ሲከስ ተከታትየዋለሁኝ። በዚህም መሰረት በእውቀቱ ስዩምም ላይ የተሰነዘረው ክስና ወቀሳ የተለመደው የአቶ አሰፋ ጫቦ መሰረት የሌለው ከስና ወቀሳ አካል አድርጌ ወስጀዋለሁኝ። ሙሉውን ያንብቡ