(ከባላንገብ) – ኢሕአፓ የሚታገለዉ ለህግ የበላይነት ነዉ በመሆኑም ተተቸሁ ተጠየኩ አላለም አይልምም። ነገር ግን ብዙ ጊዜ የሚስተዋለዉ፣ የተጎዳዉን የሞተዉን፣ ሰቆቃ የደረሠበትን፣ ስየል የተፈፀመበትን፣ ለማሰብ የሚከብድ ስቃይ የተቀበለዉን፣ ተበዳዮን ሟቹን እና ተጉጅዉን ኢሕአፓን እንከሳለን፣ እንጠይቃለን የሚሉት፣ አንድም እራሳቸዉ ተጠያቂ መሆን የነበረባቸዉ ወንጀለኞች ናቸዉ። አለያም ተጠያቂነትን በዉርስ የተቀበሉ የሚመስላቸዉ እና ኢሕአፓ እራሱን መከላከል አልነበረበትም የሚሉ ቂሎች ናቸዉ። በወታደራዊዉ ደርግ ስየል የፈፀሙም ሆነ የወያኔ ባለሟል ሆነዉ በወገኖቻችን ደም የነገዱትን ከሃዲወች ለፍርድ የማቅረቡ እና የህግ የበላይነትን በተግባር የመተርጎሙ ጉዳይ በወያኔ ዉድቀት ማዕግስት በይደር የማይያዝ እና የማይታለፍ ሃገራዊ ግዴታ ነዉ። ያኔ ብቻ ነዉ ወደ ስልጣን መንበር የሚመጡ ሁሉ ለተግባራቸዉ ተጠያቂነትን እንዲቀበሉ ማስገደድ የሚቻለዉ። በርግጥ ይህ ሃሳብ የሚያንዘረዝራቸዉ የዕብድ ገላጋዮች ቁጥራቸዉ ትንሽ አይደለም። ሺፍንፍን ለምግብ እንደሆን እንጅ በሃገር ጉዳይ ቦታ የለዉም። ሙሉውን ጽሁፍ ያንብቡ