ዴሞ የኢሕፓ ልሳን (ቅጽ 41 ቁ. 1 መስከረም 2013 ዓ.ም) – . . . አሮጌው ዓመት አልፎ መስከረም ሲጠባ በሥሙ እየማሉና እየተገዘቱ መልሰው እሱኑ ሲያስፈራሩትና ሲገድሉት፤ ሲያስርቡትና ሲያፈናቅሉት መኖራቸውን አውቆና ተረድቶ ሕግና ሥርዓት ሲጣስ፤ ሰብአዊ መብቶች ሲጨፈለቁና ፍትህ ሲጓደል ዝም ብሎ ካየ “ከትናንቱ ምን ተማረ?” ያሰኛልና ከተጠናወተን ሕመም ለመፈወስ መድኅኒቱ በአዲስ ዓመት በአዲስ የትግል መንፈስ ጥንካሬን ተላብሰን፤ ከፍርሃት ተላቀን እውነትን ለመናገር የሚደፍር አዕምሮና ልሳን፤ አምባገነኖችን የሚታገል ቆራጥ ወኔ ሊኖረን ይገባል።
ሕዝብንና አገርን የሚጎዳ ስብዕናን የሚነካ እና የሚያዋርድ ተግባር በአጋርና በሕዝብ ላይ ሲፈፀም እያየን ዝም ከማለት ለፍትህና ለሰብዓዊ መብቶች መከበር መነሳት ለአሁኑ ብቻ ሳይሆን ለመጪው ትውልድና ለታሪክ በጎ ነገር ትቶ ለማለፍ ይረዳልና በአዲሱ ዓመት በአዲስ የትግል መንፈስ አገራችንና ሕዝባችንን በጋራ እንታደግ። ሙሉውን ጽሁፍ ያንብቡ . . .