በፍኖተ ዴሞክራሲ የኢትዮጵያ አንድነት ራዲዮ – በሀገራችን የቅርብ ጊዜ የፖለቲካ ታሪክ ላይ ብቻ ስናተኩር፤ የተፈራረቁት መሪዎች ሁሉ፤ ሕዝባቸውን በሚገባ ሳያውቁ፤ ሕዝቡም እነርሱን ሳያውቃቸው፤ ሕዝቡ እየተገዛ፤ እነርሱም እየገዙ ማለፋቸውን መረዳት ይቻላል። ሕዝቡን ሳያውቁት ሥልጣን ይዘው፤ ሳይረዱት ገዝተው፤ ሳይወዱት -ሳይወዳቸው፤ሳያቀርቡት- ሸሽቷቸው፤ ተኮራርፈውና ተቀያይመው ይለያያሉ። ሳይተዋወቁ የኖሩ በመሆናቸው፤ ባዕዳን እንጅ የአንድ ሀገር ዜጎች ሳይሆኑ ይቆያሉ። “የማያውቁት ሀገር እንደማይናፍቅ” ሁሉ፤ እነርሱም በሚገባ ባለመተዋወቃቸው ምክንያት በሚለያዩበት ጊዜ መነፋፈቃቸው ቀርቶ፤ እንዲያውም “እንኳን ተላቀቅን” ብለው፤ ዳግመኛ እንዳይገናኙ ተማምለው ተነጣጠለው ይለያያሉ። ሙሉውን ጽሁፍ ያንብቡ