ከአምሳለ ዓለሙ: የመገናኛ ብዙሃን፦ የሕትመት ውጤቶች (ጋዜጣና መጽሔት)በሬድዮና በቴሌቭዥን የሚተላለፉ እንዲሁም በኢንተርኔት የሚደረጉ የመረጃ ልውውጦች ማለት ነው። የሃሳብ ነጻነትና የመገናኛ ብዙሃን መከበር የመብት ጥሰቶችን ለማጋለጥና ለዲሞክራሲያዊ ሥርዓት መሰረት ነው። ሀሳብን በነጻ የመግለጽ ነጻነት ለሰው ልጅ የተሰጠው ተፈጥሮአዊ ችሮታ ሲሆን ሰብአዊ መብትንና ክብርን የማስጠበቂያ መሳሪያ ነው። ዜና የማግኘት መብት መኖር በተለያየ ደረጃ ለመልካም አስተዳደር መስፈን፣ የመንግሥት ተግባር ግልፅነትና የተጠያቂነት ግዴታ እንዲኖርበት አስተዋፅዖ ያበረክታል። በተለያዩ የመንግሥት ተቋማት ውስጥ የሚገኙ ችሎታ ቢስ ባለሥልጣናትን በነቂስ ለማውጣት፣ የሀገር ሀብት በባለሥልጣናት እንዳይባክን በአባላቱም እንዳይዘረፍ ነቅቶ ለመጠበቅና ለመከታተል፤ ከዚሁ ጋር በማያያዝም ሙስናን፣ ፍርደ ገምድልነትን፣ አድሎዎአዊነትን ለማጋለጥ ይረዳል። ከዚህ በተጨማሪ የተቀላጠፈ አስተዳደር ሂደትና የእድገት ጅማሮዎች ለፍሬ እንዲበቁ እንዲሁም ለተሻለ የኤኮኖሚ፣ የአስተዳደር አገልግሎትና ለተሻለ የሕግ ዋስትና መሰረት ይጥላል። ሙሉውን ያንብቡ …