ሀማ ቱማ፡ እውነቱን ለመናገር ታላቁን የኪነት ሰው ጋሼ ብዬው አላውቅም። ኃይሉን ኃይሉ ወይም ገሞራው ነበር ብዬ የምጠራው።የነበረኝ አክብሮት ግን ቅንጣትም ሳይቀንስ። ገሞራው ያኔ በዚያ ጊዜ ለእኛ ወጣቶቹ ዕንቁ አርአያችን ነበር። ተራማጅ የኢትዮጵያ ተማሪዎች አንቀሳቃሶች፤ የመሬት ለአራሹ ሰልፍ አቀነባባሪዎች ተብለው ከዩኒቨርስቲ ከተባበሩት ዘጠኞች አንዱ ነበር። ዝነኛው ነበር። በ1959 ዓ. ም. ደግሞ ‘’በረከተ መርገም’’ን ገጥሞ ዳግም ከስር ዓቱ ሲጋጭና ችግር ሲገጥመው ገዘፈ። ሙሉውን ያንብቡ …